+251 116 479 500/04 +251 911 516586 info@bigetaplc.com
  • News & Events
  • FAQ
  • Vacancy
  • Facebook
  • YouTube
  • LinkedIn
Bigeta Business PLC.
  • HOME
  • ABOUT BIGETA
    • Mission, Vision & Values
    • Our Team
    • Partners & Stakeholders
    • Our Process
  • SERVICES
    • Construction of Water Supply
    • Construction of Sewerage & Wastewater Treatment
    • Infrastructure
      • Construction of Irrigation & Dam
      • Construction of Road & Bridge
      • Construction of Building
    • Electromechanical Equip Supply & Installation
    • Pipe & Fittings Supply
    • Equipment Import & Rental
    • Real Estate
    • Design Review Services
  • PROJECTS
    • Water Supply Projects
    • Sewerage & Wastewater Treatment Projects
    • Irrigation & Dam Projects
    • Road and Bridge Projects
    • Building Construction Projects
    • Electromechanical Equip Supply & Installation
    • Design Review Project
  • QUALITY
  • HSE POLICY
  • SOCIAL RESPONSIBILITY
  • CONTACT US
Select Page

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር በጋራ በ22 ከተሞች ከሚያሰራቸው የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክቶች (Faecal Sludge Treatment Plants) መካከል የአርባምንጭ ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ላይ ከሚገኑት አራት ፕሮጅክቶች መካከል አንዱ መሆኑ ተገለፀ።

by admin | Feb 9, 2026 | Uncategorized | 0 comments


Ministry of Water and Energy – Ethiopia 

https://www.facebook.com/share/p/18HUZpdvqt

የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክቶች( Faecal Sludge Treatment Plant) ተገንብተው ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ጥር 28/2018ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአለም ባንክ ጋር በጋራ የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታቸውን በጥሩ አፈጻጸም እያከናወኑ ላሉ አራት ከተሞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠናው መክፈቻ የሳኒቴሽን መሠረተ ልማት መሪ ሰራ አስፈጻሚ አቶ ኑረዲን ሙሃመድ በሁለተኛው የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት በርካታ ሰራዎች መከናወናቸውን ገልጸው በተለይም ለሳኒቴሽን መሠረተ ልማት በተሰጠው ትኩረት በርካታ መዋለ ንዋይ ፈሶባቸው የተገነቡ ፕሮጀክቶች ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክቶቹ ተገንብተው ሲጠናቀቁ የሚጠበቀውንና የሚፈለገውን አገልግሎት እንዲሰጡ ዘላቂነታውን ለማረጋገጥ የአቅም ግንባታ ስልጠናው ወሳኝ ነው ብለዋል።

በዚህ ፕሮጀክት የተጀመሩትን ስራዎች በቀጣይ እያሰፋን መተግበር ይጠበቅብናል ያሉት አቶ ኑረዲን ዛሬ የተጀመሩ ሰራዎች ሲጠናቀቁ ወደ ሌሎች ከተማዎች እያሰፋን ከተማዎችን ለነዋሪዎች ምቹና ማራኪ ለማድረግ ከፍሳሽ ጋር የተያያዙ ሰራዎችን በአግባቡ ማስተዳደር ይጠበቅብናልም ብለዋል።

የዛሬው የውይይትና የስልጠና መርሃ ግብር ዋና አላማም የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ዘላቂነት ከማረጋገጥ አኳያ ምን ማድረግ እንዳለብን፣ በቀጣይ እንዴት መተግበር እና ማጠናቀቅ እንዳለብን መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ነው ብለዋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሳኒቴሽን መሠረተ ልማት ክትትልና ድጋፍ ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ኃ/ሚካኤል በሁለተኛው የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ባለፉት አመታት በ22 ከተሞች የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ሲሆን ጥሩ አፈጻጸም ያሳዩ ጅማ፣ አርባምንጭ ፣ሻሸመኔና ወላይታ ሶዶ ከተሞች አተገባበራቸው ምን መሆን እንዳለበት የቢዝነስ እቅድ አዘጋጅተው ወደ ተግባር ሊገቡ የሚያስችላቸውን ስልጠና ከአለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር በመተባበር ስልጠናው መሠጠቱን ነግረውናል።

እየተገነባ ያለው የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት እንደመሆኑ ከመነሻው ጀምሮ ትስስሩ ምን እንደሚመስል ፣ እንዴት እንደሚመራና የገንዘብ ወጭው በምን መልኩ መሸፈን እንዳለበት ወጭና ገቢን በግልጽ የሚያሳይ እና በዛላቂነት ማገልገል የሚችል የቢዝነስ እቅድ እየተዘጋጀ መሆኑንም ገልጸዋል ።

ፕሮጀክቱ በአለም ባንክ ድጋፍ የሚተገበር ነው ያሉት ዴስክ ኃላፊዋ የተዘጋጀው የቢዝነዝ ንድፍ እቅድ ገንቢ ሀሳቦችና ማሻሻያዎች ተጨምረውበት በየከተሞቹ ሊተገበር የሚችል ያለቀለት የቢዝነስ እቅድ ለማዘጋጀት የዛሬው የስልጠና መድረክ አጋዠ ነውም ብለዋል።

በእለቱ አራቱም ከተሞች የተዘጋጁ ንድፍ የቢዝነስ እቅዶች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በነገው እለትም በሌሎች ከተሞች እየተተገበረ ባለው የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት የቢዝነስ እቅድ ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል።

በመድረኩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዘርፉ ሀላፊዎችና ሙያተኞች ፣ የክልል የዘርፉ ሙያተኞች ፣ የአለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ተሳትፈዋል።

Submit a Comment Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent Posts

  • Awash Sebat Town Water Supply and Sanitation Project Successfully Completedand Commissioned by BIGETA Business PLC.
  • የከተሞችን የሳኒቴሽን ደረጃ ለማሻሻል የሚያግዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
  • የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር በጋራ በ22 ከተሞች ከሚያሰራቸው የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክቶች (Faecal Sludge Treatment Plants) መካከል የአርባምንጭ ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ላይ ከሚገኑት አራት ፕሮጅክቶች መካከል አንዱ መሆኑ ተገለፀ።
  • Christmas Greetings from BIGETA
  • Foundation Stone Laid for Adama Town Faecal Sludge Treatment Plant; BIGETA Business PLC Awarded Construction

Recent Comments

  1. Yonas Muluneh on ከ 4.6 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በአዳማ እና በባህርዳር ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያና ማስወገጃ ግንባታ ውል ስምምነት ተደረገ፡፡
  2. Abraham Yisehak on BIGETA Business PLC. Reinforces Quality Standards with ISO 9001:2015 Refresher Training
  3. Mehidi Hussien on Bigeta Business PLC Signs Contract Agreement with the Ministry of Water and Energyfor the Construction of Dimeka Town Water supply Project

Latest News/Events

Awash Sebat Town Water Supply and Sanitation Project Successfully Completedand Commissioned by BIGETA Business PLC.

Awash Sebat Town Water Supply and Sanitation Project Successfully Completedand Commissioned by BIGETA Business PLC.

Quick Links

  • Construction Solution
  • EM Equipment Supply & Installation
  • Pipe & Fittings Supply & Installation
  • Real Estate Development for Sale & Rent
  • Equipment Supply, Import & Rental

Follow Us

  • FollowFollow
  • FollowFollow
  • FollowFollow
  • FollowFollow
Profile Picture

BIGETA Business P.L.C.

Typically replies within an hour

BIGETA Business P.L.C.

Hey there 👋

How can I help you?

Telegram Start Chat

Contact Us

Lemi Kura Sub- city, CMC Road
Golgota Bldg. Floor 8th,
Addis Ababa, Ethiopia

+251 116 479 500/04

+251 911 516586

info@bigetaplc.com

 www.bigetaplc.com

© 2025 Copyright by Bigeta Business PLC. All rights reserved.

  • CONTACT US
  • Vacancy
  • Privacy Policy